ኦሮሚያ ሬድዮና ቴሌቭዥን ድርጅት 20 ጋዜጠኞች ከስራ ታገዱ

As Addis Admass newspaper writes quoting sources, twenty ORTO (Oromia Radio and Television Organization) journalists are banned from work for the alleged “Narrow minded political attitude” in connection with the assessment session it had on the issue of the Addis Ababa integrated master plan. 

It is remembered that a discussion was held in April, 2014 at the Adama city on the topic of the Addis Ababa integrated master plan where the region’s politicians, journalists and higher officials participated. The discussion and assessment sessions were also conducted following the region wide violence in protest to the integrated master plan. 

As sources told the newspaper, lots of journalists were expressing their idea and concern on the integrated master plan at the April’s discussion session and during the two-months long training given to the journalists. 

Addis Admass writes that twenty ORTO journalists are prohibited from entering into their office on Wednesday and the journalists told the newspaper that expressing their idea on the training sessions must have been the reason behind their ban from work. 

Girum Tebeje of DireTube from Addis Admass

የኦሮሚያ ሬድዮና ቴሌቭዥን ድርጅት 20 ጋዜጠኞች ከስራ ታገዱ

*‹‹ሃሳባችንን በነጻነት በመግለጻችን ነው ከስራ የታገድነው››፡፡ የታገዱት ጋዜጠኞች

ከአዲስ አበባና የዙሪያዋ ልዩ ዞኖች ማስተርፕላን ጋር በተያያዘ የኦሮሚያ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ባካሂደዉ ግምገማ 20 ጋዜጠኞችን ‹‹ጠባብ የፖለቲካ አመለካከት አላችሁ›› በሚል ገምግሞ ከስራ ማገዱን ምንጮች ገለጹ ሲል አዲስ አድማስ ጋዜጣ አስነብቧል፡፡

በማስተር ፕላኑ ዙሪያ በሚያዝያ ወር ፖለቲከኞች ፣ ባለስልጣናትና ጋዜጠኞች የተሳተፉበት ውይይት በአዳማ ናዝሬት ተካሂዶ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ፣ በማስተር ፕላኑ ዙሪያ በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ዪኒቨርሲቲዎች እንዲሁም በርካታ ከተሞች ተቃውሞና ረብሻ ከተከሰተ በኋላም ስብሰባዎችና ግምገማዎች በብዛት ቀጥለዋል፡፡

በሚያዚያ ወር በተካሄደው የአዳማ ውይይት ላይ ማስተር ፕላኑን በተመለከተ በርካታ ጋዜጠኞት የተለያዩ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን አንደሰነዘሩ የጠቀሱት የጋዜጣው ምንጮች ፤ በማስተር ፕላኑ፣ በወቅታዊ ጉዳዮችና በሚዲያ ነጻነት ዙሪያ ለሁለት ወር በዘለቀው የጋዜጠኞች ስልጠና ላይም ተመሳሳይ ሃሳብና ጥያቄዎችን አንደተሰነዘሩ ገልጸዋል::

ስልጠናው ከተጠናቀቀ በኋላ ባለፈው ረቡዕ ወደ ስራ ሊገቡ ሲሉ ወደ ግቢው አትገቡም ተብለው መከልከላቸውን የጠቀሱት ጋዜጠኞቹ በስልጠናው ላይ በተነሱ ወቅታዊና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ሃሳባችንን በነጻነት በመግለጻችን ነው ከስራ የታገድነው ሲሉ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል፡፡

ከስራቸው የታገዱት ጋዜጠኞች የጸጥታ ሃይሎች በማስተር ፕላኑ ምክንያት የተነሳውን ረብሻ በጥይት ሳይሆን በአስለቃሽ ጭስ መቆጣጠር ነበረበት ብለን ተናግረናል ማለታቸውንም ጋዜጣው አትቷል፡፡

ጋዜጣው የኦሮሚያ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅትን ጋዜጠኖቹን ያገደበትን ምክንያት ለመጠየቅ ያደረኩት ጥረት አልተሳካልኝም ብሏል፡፡

Source: http://www.diretube.com/articles/read-20-orto-journalists-banned-from-work_5629.html#.U68oo0DDvIU

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s